ኮሜዲያን እሸቱ በሶሻል ሚዲያ ከስድስት ነጥብ አምስት ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሉት በበጎ ስራዎቹም ብዙ ለውጦችን ለማምጣት የቻለ ወጣት ተጽእኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከቪዲዮ ኤዲቲንግ ጋር በተገናኘ የአስራ አምስት አመታት ልምድ ያለው ባለሙያ ነው። ቪዲዮ ኤዲቲንግን ከ ከኒውዮርክ ፊልም አካዳሚ ጀምሮ ከፍተኛ አለም አቀፍ ተቀባይነት ካላት የፊልም ባለሙያ ከይዘሮ አይድ አሸናፊ ጋር ለአራት አመታት ያህል አብሮ በመስራት ከፍተኛ የኤዲቲንግ ልምድ ያዳበረ ሲሆን በዶንኪ ቲዩብ ደግሞ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ቪዲዮዎችን በማምረት እና ከአምስት መቶ ሚሊየን በላይ እይታዎችን በማግኘት ከፍተኛ የኤዲቲንግ ልምድና እውቀቱን ሊገነባ ችሏል፡፡ በዚህም መሰረት ኮሜዲያን እሸቱ በ2015 ዓመተ ምህረት ዶንኪ አካዳሚ በሚል ልምድና እውቀቱን ለማካፈል ባቋቋመው የትምህርት ፕላትፎርም ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎችን በዩቲዩብ አሰልጥኖ በሰርተፊኬት ያስመረቀ ሲሆን አሁን ደግሞ የኤዲቲንግ ትምህርትን በኦንላይን እና በአካል መስጠት ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን የኦንላይን ስልጠና ተቀላቅላችሁ የዘመኑ ምርጥ ባላሙያ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡
በእኛ አጠቃላይ የቪዲዮ አርትዖት ኮርስ ውስጥ የሚማሩትን ያግኙ
የኛ ሁሉን አቀፍ ሥርዓተ-ትምህርት በቪዲዮ አርትዖት ኮርስ ላይ ስኬታማ ለመሆን የሚፈልጉትን ሁሉ ይሸፍናል።